»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Wednesday 1 January 2014

conference 2014

እንኳን  ወደ conference 2014 በደግ መጡ።


ኮንፈረንሱ በስተግራም በስተቀኝም ጀምሯል።

ቃልም እንካፈላለን፣እርስዎም እንዲያካፍሉ ይጠበቅብዎታል

የጸሎት ጊዜ ይኖረናል ፤እርስዎም ፤እንዲጸልዩ በትህትና ይጋበዛሉ።

የመዝሙር ጊዜም አለ ፣የተጋበዘው ዘማሪ ሚስጥር ነው  ታዋቂ ዘማሪ ተጋብዟል (አሁን አንነግርዎትም ሚስጥር ነው ወደ ኮንፈረንሱ የዘለቁ እንደሆነ ያገኙታል )

የስነጽሁፍ ጊዜ አለ።ሰካራሞች ሊኖሩ ይችላሉ።ሰክረው የማውቁም ይሰክሩ ይሆናል አይታወቅም።

የወንጌል ስርጭት ጊዜ ይኖረናል - ወደ አራዳ ወርደን  የሰማነውን እናሰማለን እንጂ እየሰማን ብቻ አንኖርም።

“የሰማውን ያመነ አለማሰማት ያዳግተዋል” 
-አንድ ወንድም ለወንጌል ስራ ቅስቀሳ የጠቀሰው::

ወንድማለም የሰማውን ስላመነ ለማሰማት ወሰነ

***
እንኳን  ወደ ሔዋኔ ወልደመለኮት ልዩ ኮንፈረንስ በድጋሚ በደግ መጡ።
***
አሁን የኮንፈረንሱን መግቢያ ሙዚቃ እንዲያዳምጡ በትትና እንጋብዝዎታለን :
***
እርግጥ እኮ ነው ኮንፈረንሱ በስተግራም በስተቀኝም ጀምሯል።

የተጋበዘው ታዋቂ ዘማሪ :  እርስዎ እራስዎ።
\እኔ ታዋቂ ዘማሪ እንኳ ልሆን መድረክ ላይ ወጥቼ አላውቅም ካሉ መዝሙር መቶ ሃምሳን ከቁጥር ፩ - ፮  ካነበቡ ሰንብተዋል ማለት ነው /


ኮንፈረንሱ ቀጥሏል።

የብላቴናው  አማተር ሪል ማተር  መዝሙሮች በሚለው መጀመር ይችላሉ።


የኮንፈረንሱ ፕሮግራም መሪ - እኮ  ማነው ? : ከእርሶ ሌላ ማን ሊሆን።

***
የታመሙ እንጠይቃለን ፣የታሰሩ እስፈታለን፣ለተንሸራተቱ የመዉጫ መሰላል እንልካለን(ሌሎች ለኛ እንዳደረጉት እነሆ ሆነ ዛሬ የኛ ተራ)


ስለተለያዩ ችግሮች እንጸልያለን።

ከችግር በላይ የሆነ አንድ ብቻ በሰማይ የሚኖር ወደ እርሱ በትህትና ማስተዋል እንጮሃለን እንጂ እርስ በእርሳችን አንጯጯህም።

ስለአገር ጉዳይ እንጸልያለን ፡አገሩን የማይወድ ላገሩ ምን ይረባል።ለጎረቤት አገሮች ሁሉ እንጸልያለን ፡የእነርሱ ሰላም እና በጎ መሆን ለኛም ይጠቅመናል።

ኮንፈረንሱ በስተግራም በስተቀኝም ቀጥሏል።

የወይን ጠጅ ያረጀ መጠጣት እሻለሁ ካሉ - እንዴ እርስዎ ሰካራም ነዎት እንዴ? ምነው አሉ? ፍቅር በስተርጅና  ይዞኝ ነው አሉ 

ይሁና

ወደመለኮት ልጆች የሚዲያ ጣቢያ በመታደም የሰሞንኑ ዜናዎች፣የመንግስትን አቋም መግለጫዎች እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የወጡ መለጫዎችን ከጦርነት ድል ወሬዎች ጋር አክለው መስማት ይችላሉ።

ጥቅሶችን ላንብብ ፣የጥንት ዘመን እና ያሁን ዘመን መዝሙሮች ድንገት ሳላስበው ትዝ እያሉኝ ነውና በልቡናዬ ላዚማቸው ካሉም መብትዎ ነው::

የለም የለም  ዘና ብዬ መንፈሳዊ ግንዛቤየን ልታዘበው ካሉም ደግሞ እልም አለ ባቡሩ እና ሌሎችም ወሳኝ ጥያቄዎች  ወደተሰኘው ወገን ጎራ ማለት ነው።

የታመሙ ሆስፒታል ሄደን እንጠይቃለን እንጂ ጌታ ሆይ ማራቸው ፈውሳቸው ብለን ቸርች አንቀርም::

አንድ ወንድም ድንገት ሳናስበው ከጉባኤው መሀል በእጁ ምልክት በማሳየት መናገር እሻለሁ ስላለ እናዳምጠው:



እ አው አመሰግናለሁ (እናንተን አይደለም) ጌታን አመሰግናለሁ - ይህን ዕድል 
ስላገኘሁ አው መር የምፈልገው እ ሆስፒታል ሄደን የታመሙ እንጠይቅ ፤
ወህኒ ወርደን (ሄደን ማለቴ ነው ) እ አው የታሰሩ እንጎብኝ በሚለው ላይ 
ትንሽ መጨመር ፈልጌ ነው ...ባለፈው አንድ ወንድም ያደረገው
 በጎ ተግባር ለኛም ምሳሌ ይሆናል ብዬ ነው :: 


(እሺ ወንድም እናመሰግናለን የራስህን ምስክርነት ብቻ ብትናገር ...አንድ ወንድም ያደረገው በጎ ነገር ካለ እራ ቢመሰክር። ከይቅርታ ጋር ወንድማችን በብዙ ትትና ነው የምንጠይቅህ እንዳትቀየመን።)


አይ እኔ ስለራሴ የምመሰክረው የለኝም ወንድሜ ያረገውን በጎ ነገር ነው 
ልመሰክርለት  የምሻው እ ይቅር ካላችሁም ይቅር::
መቸም በጎ ነገር ማየት መስማት ማንበብ የማይወድ ክፉ ብቻ ነው::


(እሺ ወንድማችን ቀጥል)


...አው እና ያ ወንድም ጎረቤት ሰው ጋር ሄዶ እንዴ ከዚሁ ቀያችን ውስጥ 
ታሞ ሆስፒታል የተኛ ሰው አለ አደለም እንዴ? 
ሂደን እንጠይቅ እንጂ ብሎ ባለፈ ቅዳሜ ለት  ከጎረቤት ሰው 
አስተባብሮ ሆስፒታል ጉዞ ጀመሩ ።
እና ከዚያም እያዘገሙ እየተጫወቱ ሲሄዱ ሆስፒታል ከሄድን 
አይቀር ለምን ዘንቢል ይዘን አንሄድም ሲል አሰበ:: ከዚያም ዘንቢል 
ሆስፒታል ሄዶ ምን ይረባል የሚል ሀሳብ መንዘሩ 
ስለማይቀር አይ ለታመመ ሰው የሚሆን ብርቱካን መንደሪን ብናና
 እናኖርበታለን እንጂ በሚለው አሳብ ስምምነት እያዘገሙ 
እየተጫወቱ ሲሄዱ ...አይ አንድ ፊቱን ሆስፒታል ድረስ ፒስታል 
ሙሉ ብናና ብርቱካን ጁስ ይዘን ከሄድን አይቀር ለምን 
የጌታን የኢየሱስን ፍቅር የሚያስረዱ የደህንነት የፈውስ 
በራሪዎች አንሰውርበትም ሲል ምክር ጠየቀ።

ሆነም ደረስም አለፈም

 ከዚያም ሊወጡ ሲሉ ያ ንድም  ድንገት አሰበውና
 መንፈሳዊ ነገር በዉነት ፍጹም ግልጥነት ነው 'ንጂ 
በስውር የሚደግ ሴራ የለውም ብሎ ድንገት ስላሰበ - "ወንድሞች  እህቶች
 ያመጣንላችሁን  ፍራ ፍሬ ጁስ ልትወዱት 
ዘንድ እንድትችሉ ተስፋ ናደርጋለን- በመያዣው
 ፕላስቲክ ፔስታል በሚሉትም ዘንቢል ውስጥ የሚነበቡ ትራክቶች 
አኑረንላችኋል " ብለው በአንድ ወፍ ሁለት ድንጋይ ላይ አርፈው ተመለሱ ::
አው እና ለማለት የፈለኩት ያ ወንድም አው ይህ ወንድም 
ጸጋው በዝቶለት ምህረት ተከትሎት ፍቅር ደግፎት እንዳለው ... 
እንዳደረገው...እኛም ደግሞ በየበኩላችን በየበኩላችን 
የታመሙ እንጠይቅ ለጌታ አምላካችን። ...ከኛም ወገን ደግሞ አ
ንዳንዶች  የቻልን የታሰሩ እንጎብኝ...ለማለት የፈለኩት




ኮንፈረንሱ ቀጥሏል :: 

የምስክርነት ጊዜም አለን ማለት ነው::

የአስራት የመባ የስጦታ ጊዜ ይኖረናል።(አይኑረን ካሉም ይቀራል)ኮንፈረንሱ ቀጥሏል።

ነውና የምኖረው ዳያስፖራ በሚሉት አገር እናም ሆኖም ፈረንጅኛ ነው የሚቀናኝ ፣ፈረንጅኛም ብቻ የሚችሉ የተማሪ ቤት እና የስራ ቦታ ወዳጆች አሉኝ ካሉ ደግሞ ለርስዎ ሲባል ወደተዘጋጀው እና The Mountain of Honeypoems ወደተሰኘው መስክ ጎራ እንዲሉ በብዙ ፍቅር እና ትትና እንመክርዎታለን።

ኮንፈረንሱ በስተግራም በስተቀኝም ቀጥሏል።


ወደተዘጋጀልኝ ኮንፈረን በመምጣቴ እጅጉን ተደስቻለሁ ፣ ተባርኬአለሁ  ጌታ መልካም ነው ፣ ይህንንም በጽሁፌ አረጋግጣለሁ ካሉ እጅግ በጎ ነገር ብለዋ። እንግዳዬ ነዎት በተሰኘው  የእንግዶች አስተያየት መስጫ (Guest Book) ላይ ብእርዎን ሊያሰፍሩ ነው ማለት ነው።

መጸለይ ነው የምሻው - ለርስዎ ለራስዎ ወይምለኔ ለራሴ - ካሉ እጅጉን መልካም ኣስበዋል 4me ወደሚለው እባክዎ ይጓዙ ።

 ***
ኧርነታችን (ኮንፈረንሱ)  በዚህም በዚያም መልኩ ቀጥሏል።
 ***

ክብር ለዘለዓለም ክብር ለስሙ ።
አዘጋጅ እና ተላላኪ ብላቴና  (አገልጋይ)  : ብላቴናው ዘመድዎ።
ለክብሩ ምስጋና።
“When you produce much fruit, you are my true disciples. This brings great glory to my Father.
- Jesus Christ.
(John 15:8 New Living Translation )


No comments :

Post a Comment

Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።