»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Monday 1 April 2013

ሬማ ማንቼ AIR Ways


****

ሬማ ማንቼ AIR Ways: Going Great Miles To Praise The LORD.

 ።።።

 

Cabin Crew:(ፈጠን ቀጠን ቀልጠፍ ባለ የሆስተስ ድምጽ ምሳሌ) :

ክቡራን እና ክቡራት መንገደኞቻችን በሬማ ማንቼ  Air Ways ስም እንኳን ደህና መጣቹ በማለት የማስተናግዳች እታለም ግርማቸው  ነኝ፡፡

በዛሬው ዕለት ይዘውን የሚበሩት  ካፕቴይን አያሌው ምህረትቸርነቱ ሲሆኑ ረዳት አብራሪያቸው  ሻምበል ወንድማችን መልካምሰው ናቸው፡፡

ፕሌ ኑ ቴክ ኦፍ ሊያደርግ ስለሆነ ክቡራን እና ክቡራት  መንገደኞቻችን ቀበቷችሁን እንድታስሩ በጥብቅ  ትህትና እንጠይቃለን፡፡

***

ካፕቴይን አያሌው :
(በጎርናና ወፍራም ጀንተል ያለ የካፕቴይን ድምጽ ምሳሌ)

ዚስ ኢዝ ካፕቴይን አያሌው ምህረትቸርነቱ ስፒኪንግ ፍሮም ፍላይት ሩም .... እ...ኣው - ይህ ካፕቴይን አያሌው ነው የሚናገረው ::ካፕቴይን  አያሌው  በድጋሚ በሬማ ማንቼ Air Ways፣በረዳት አብራሪያቸው በሻምበል ወንድማችን መልካም ሰው፣
እንዲሁም ደግሞ  
በ Cabin Crew የስራ ባልደረቦቻችን ስም በድጋሚ እንኳን አውሮፒላናችን ላይ ወጣቹ ወይም ተሳፈራቹ በማለት ሰላምታዬን አቀርባለሁ፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከባሕር ወለል በላይ ብዙ ሺህ ጫማ ከፍ ብለን በመብረር ላይ እንገኛለን::

የአየሩ ሁኔታ መልካም እና ብርሃናማ ነው:: በጥቂቱ ከፊል ደመናማ ሲሆን ጥቂት ቆይቶ ጥርት ሊል ይችላል፡፡ሰማይ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡

***

Cabin Crew:  
ከበረራ መስተንግዶ ክፍል በድጋሚ እታለም ግርማቸው ነኝ::

ክቡራን እና ክቡራት  ቀበቷችሁን አሁን መፍታት ትችላላቹ፡፡ ጥቂት እልፍ ብለን  ሻይ ቡና እንዲሁም የሬማ ማንቼ Air Ways  ስናክ እና ቀለል ያሉ የሚቀመሱ ነገሮችን ያቀርብላችኋል፡፡


በዚሁ ሂደት ሬማ ማንቼ Air Ways ለዕለቱ  የመረጠላችሁን ሙዚቃ ይጋብዛችኋል፡፡


***

ካፕቴይን  አያሌው:
ክቡራን እና ክቡራት ከበረራ ክፍል በድጋሚ ካፕቴይን  አያሌው ይናገራል፡፡

አሁኑ  ሰዓት አየሩ ጥሩ ሲሆን ወደ ማረፊያችን እየተቃረብን ነው::

ፊታችሁን  ወደግራ  እንዲሁም  ወደቀኝ ዘወር በማድረግ ልዩ ልዩ
የአየር ጸባይ ሁኔታዎችን እና የመልክአ ምድር አቀማመጦችን ማየት ትችላላቹ፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአመፃ ኮረብቶች በመገረም ፣ የትዕቢትን ኩሬ እና የቅጥፈትን ጅረት በስተግራ በመተው ፣የጨለማውን ዓለም ከበስተኋላችን በከባድ ርቀት በመለየት ፣የአመፃን ባሕር ተሻግረን ፣ የክፋትን ውቅያኖስ አቋርጠን   አደገኛ ተራሮችን በስተግራ በመተው ፣ የጥፋትን ሸለቆ  በደመና የሕይወት ክንፎች ተሻግረናል::

********
Cabin Crew:

ክቡራን እና ክቡራት :


ወደ His Mercy Endures Forever International Airport  ስለተቃረብን እና ወደ እረፍት Run Way  ዲሰንት እያደርግን ስለሆነ ወገባችሁን በእውነት ቀበቶ እንድታጠብቁ ፣ በመዝናናት እንዝላልነት የፌዝ ጎዳና ላይ ያላቹ አርፋቹ እንድትቀመጡ እያሳሰብን ፣ሬማ ማንቼ Airways ከእኛ ጋር ለመጓዝ በመምረጣቹ  ምስጋናውን እያቀረበ መልካም ቀን ይመኝላችኋል፡፡
___________________________________

*** *** *
እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ
ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን
የምንሰብከው እርሱ ነው።
 -ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:28

*** *** *
___________________________________



ከዚህ በላይ ያነበቡት ስነ/ኪነ ጥበባ መንፈሳዊ መልክት 
ለኛ ለሁላችን በሬማ ማንቸስተር ጌታን ኢየሱስን በንጹህና በቅን ልብ
በበጎም ህሊና ሁሉ ሊያመልኩ በሚወዱ ወንድሞች  ከቀረቡት ፕሮግራሞች አንዱ ነው

የ2013 የትንሳኤውን መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማደረግ::
በልጅ ወንድም ኤልያስ ይስ ሃቅ።
በዚሁ ዕለት ግሩምድንቅ የሆኑ የሕጻናት መዝሙሮች፣ጭውውቶች
ግጥሞች   መልእክቶች እና ሌሎችም ዝግጅቶች ቀርበዋል::

ክብር ለስሙ::