»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Friday 16 November 2012

ጎብኛት ተመልከታት እንበል ዘወትር አንዘምር

“ኢትዮጵያን ጎብኛት ተመልከታት በቃል ኪዳንህም አስባት ”
እንበል ዘወትር አንዘምር።

ኢትዮጵያን ጎብኛት ተመልከታት 
በቃል ኪዳንህም አስባት 
መከራዋ በዝቶ የበደሉ ብዛት 
በጭካኔ በትር ሰይጣን ቀጠቀጣት 
እባክህ አንድዬ ፈጥነህ ድረስላት 


ልጆቿ ተሰደው በአለም በሙሉ 
ጭቆናን ለመሸሽ ስደት ሲቀጥሉ 
እንደ ምናምንቴ ከመርከብ ተጣሉ 
ደግሞም የተቀሩት እርስበርስ ሲጣሉ 
አስታራቂ ሁነን ለሁሉ እንዳመሉ 


እባክህ ጌታዬ አንዴ ተመልከተን 
አንተ ካልፈለግህን ፈላጊ የሌለን 
አለም የሰለቸን የቃልህ ህዝብ ነን 
በቀራኒዮ መስቀል ልጅህን የሰጠህን 

ኢትዮጵያን ጎብኛት ተመልከታት 
በቃል ኪዳንህም አስባት

No comments :

Post a Comment

Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።